ፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ በከፋ ዞን ለሚገኙ የግብርና ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ፡፡

ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ ለከገበሬው የተቀናጀ የግብርና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ፕሮጀክቱ በከፋ ዞን ከሚገኙ 8ወረዳዎች ለተወጣጡ የግብርና ባለሙያዎች ባሳለፍነው ሳምንት በቦንጋ ከተማ ስልጠና ሰጥቷል፡፡
ስልጠናው የከፋ ዞን ግብርና መመሪያ ሀላፊ አቶ ጋዎ አባ መጫ በተገኙበት ተጀመረ ሲሆን፤ በመርሀግብሩ ላይ በዞኑ ከሚገኙ 8ወረዳዎች ለተወጣጡ የግብርና ባለሙያዎች ስለ የከገበሬው የግብርና የተቀናጀ ኤክስቴንሽን ፐሮግራም ፐሮጀክት ገለፃ ማድረጋቸውን የፕሮጀክቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ አስናቀ ሀ/ሚካኤል ገልፀዋል፡፡
በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ 1ሚሊየን ገበሬዎችን የፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ ባለቤት የማድረግ አቅድ ይዞ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው ፕሮጀክቱ በአሁኑ ወቅት በ7 ክልል ቅርንጫፍ ቢሮዎችን በመክፈት በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ ከ210 በላይ በሆኑ ወረዳዎች ውስጥ ገብቶ እየሰራ ይገኛል፡፡
የከገበሬው የግብርና የተቀናጀ ኤክስቴንሽን ፐሮግራም ፕሮጀክት ገበሬውን በቴክኖሎጂ በመደገፍ በቂ ምርት ማምረት እንዲችል እና ምርቱን ከሀገር ውስጥ አልፎ ለዓለም አቀፍ ገበያ የማቅረብ አቅም እንዲኖረው የማድረግ ዓላማ እንዳለው የሚታወቅ ነው፡፡
መረጃውን ያገኘነው ከካፋ ቴሌቭዥን ድርጅት ነው!

Leave a Reply

20 + eleven =

×